የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፤ 11ኛ የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ፌዴሬሽኑን ለተቀላቀለው፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፤ 11ኛ የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ፌዴሬሽኑን ለተቀላቀለው፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
    ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕዝብ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት ነው ያሉት ክቡር ከንቲባው 11ኛ ክልል በመሆን የተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዚህ ሥርዓት ማሳያ በመሆኑ፤ ለክልሉ ህዝቦች ሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ትግል ስኬት፤ በድሬዳዋ አስተዳደርና በራሴ ስም እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል።
    ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በመልዕክታቸው ማብቂያ “አሸባሪውን ህወሓት እና ጀሌዎቹን በኢትዮጵያዊ አንድነት ከሥር እየነቀልን፤ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መትከላችንን እንቀጥላለን” ማለታቸውን የከንቲባው ጽ/ቤት ዘግቧል።