ባለፉት ሁለት ቀናት በባቲ ግንባር 6 የአሸባሪው ቡድን የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በከሚሴ ግንባርም 6 ከፍተኛ የጠላት ጦር አመራሮች ተደምስሰዋል

    ባለፉት ሁለት ቀናት በባቲ ግንባር 6 የአሸባሪው ቡድን የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በከሚሴ ግንባርም 6 ከፍተኛ የጠላት ጦር አመራሮች ተደምስሰዋል
    ***********************
    ባለፉት ሁለት ቀናት በባቲ ግንባር 6 የአሸባሪው ቡድን የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች የተደመሰሱ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ በከሚሴ ግንባር የጣላትን ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከፍተኛ የጠላት ጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ጋር ተደምስሰዋል፡፡
    እነዚህ በፌደራል መንግስት በሃገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ከሃዲ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች ናቸው።
    በዛሬው እለት በባቲ ግንባር በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ቀደም ሲል ከነበሩ ጥቃቶች ተርፎ ለዳግም ማጥቃት ሲዘጋጅ የነበረውን ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ኋላ የፈረጠጠውን ጠላት የወገን ጦር እያፀዳ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው።
    በሌሎችም ግንባሮች ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ሲሆን የወገንን ክንድ መቋቋም አቅቶት በተናጠልና በቡድን ወደኋላ የሚሸሸው ሃይል ዘረፋ እንዳይፈጽምና ንብረት እንዳያወድም በመከላከል ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እንዲሁም እየሸሸ የሚሄደው ጠላት እጁን እንዲሰጥ እንዲያደረግ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።
    መንግስት ከፍተኛ የሆነ የእቅድ የአመራር ጥበብና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን በመቀነስ ጦርነቱን እያካሄደ ሲሆን ጠላት ግን ህዝብን በከፍተኛ ደረጃ በጦርነቱ በመማገድ ህዝብ ጨራሽ ስትራቴጂ ተከትሏል።