የድሬደዋ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በኮምቦልቻና በደሴ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የቁሳቁስ እና የምግብ ድጋፍ አደረገ

    በመድረኩ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ምክር ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው በአገር ላይ የመጣን አደጋ መከላከል የሁሉም ዜጋ የዜግነት ግዴታና ሃላፊነት መሆኑን አውስተዋል፡፡
    እንደ ድሬደዋ አስተዳደር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችም ሆነ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
    በእስልምና ምክር ቤቱ የተደረጉ ድጋፎች ዝርዝር
    ሩዝ 50 ኩንታል በብር ሲገመት 160,000 ብር
    ቴምር 250 ካርቶን በብር ሲገመት 133,000
    ዘይት 15 ካርቶን በብር ሲገመት 40,000
    አልባሳት በማዳበሪያ ብዛት 500 በላይ በብር ሲገመት 5 ሚሊየን በላይ
    ጠቅላላ ድምር 5,333000 በላይ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡