ለድሬዳዋ ነዋሪዋች ከአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በከፌስ ቡክ ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት።
በአስተዳደራችን የሚከበረው 16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል፤ መላው የድሬዳዋ ነዋሪዎች፤ የአገራችንን በርካታ ውብ ዕሴቶች በአግባቡ እንድናውቅ፤ በወንድማማችነት መንፈስ ኢትዮጵያዊ ህብረታችንን ይበልጥ እንድናጎለብት፤ እንዲሁም… የእኛ የድሬዳዋውያን መገለጫ የሆነውን፤ በፍቅር እንግዳ የመቀበል መልካም ዕሴታችንን ይበልጥ እንድናጠናክር መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል። በትውልዶች ታሪክ የማይረሳ አስነዋሪ ድርጊት የፈፀመው አሸባሪው የህወሓት አረመኔ ቡድን፤ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ ግብዓተ መሬቱ እየተፈፀመ…


