በህልውና ዘመቻ በጀግንነት አኩሪ ድል እያስመዘገበ ላለው ጀግናው የኢ/ፌደራል ፖሊስ የድ/ዳ አስተዳደር እና ድሬደዋ ፖሊስ የተለያዩ ድጋፎችን አበረከቱ::
ይህን መሰሉ ሀገርን የታደጉ ጀግኖችን የመጠየቅና ድጋፍ የማድረግ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልፃል:: በኢ/ፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ኮልፌ ማሰልጠኛ በተካሄደው የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይ ንግግር ያደረጉት የድ/ዳ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለሀገርና ህዝባችሁ ስትሉ በህልውና ዘመቻ በተሰለፋችሁበት ግንባር ሁሉ መስዋትነት በመክፈል በጀግንነት የሽብር ቡድኖች ሽንፈት እንዲከናነቡ በማድረግ ሀገራችሁን ታድጋችሃል እና ትልቅ ክብር ይገባችሃል ነው ያሉት::…


