የ ”ናፍቆት! ድሬዳዋ” የብልጽግና ፓርቲ ድ/ቅ/ቤት የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።

    የብልጽግና ፓርቲ ድ/ቅ/ቤት የጽዳት ዘመቻ፣ የችግኝ መንከባከብና የምንጣሮ ስራ የብልጽግና ፓርቲ ዋናው ጽ/ቤት የሱፐርቪዥን ቲም፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቀበሌ 03 ሴፍትኔት እና የከነማ ደጋፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
    በጽዳት ዘመቻው አመራሩ ሳይቀር ህዝቡን በማስተባበር ለበርካታ ሳምንታት ሳይቆራረጥ ባህል በማድረግ ተጠናክሮ መቀጠሉ የሚበረታታና በኢትዮጵያ ልማትና እድገት ከተሞች 53% አስዋወጽኦ እንዳላቸው አንስተው በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው የብልጽግና ፓርቲ ዋናው ጽ/ቤት ሱፐርቪዥን ቲም መሪና የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ሚ/ር ሚ/ድኤታ አቶ ሄኖስ ወርቆ ገልጸዋል።
    በመጨረሻም የመርሃግብሩ ለተሳተፉ አካላት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ምስጋና አቅርበዋል።
    ምንጭ፦ድሬዳዋ ብልፅግ
    ግንቦት 20/2014