በመልካም ስብዕና ግንባታ ላይ ያተኮረ መርሃግብር በኢትዮ ኢታሊ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተካሂዷል። በመርሃግብሩ በአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ምህረት ደበበ በአመለካከት ኃይል ዙሪያ ገለፃ ተሰጥቷል። በመርሃግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁኸርና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍና ጥሪ የተደረገላቸው የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል። በርካታ ወጣቶችም በመርሃ ግብሩ ታዳሚ ሆነዋል።


