የድሬደዋ አስተዳደር የሞዴል ህፃናት ፓርላማ 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

    የድሬደዋ አስተዳደር የሞዴል ህፃናት ፓርላማ 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት ተካሄዷል፡፡በጉባኤውም የሞዴል ህፃናት ፓርላማ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ተማሪ ሮብሰን አብዱልቃድር የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ የድሬደዋ አስተዳደር የሞዴል ህፃናት ፓርላማ ምስረታ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ቀርቦ ፀድቋል፡፡
    በመቀጠልም የድሬደዋ አስተዳደር የሞዴል ህፃናት ፓርላማ 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ2014 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የሞዴል ህፃናት ፓርላማ ፀሀፊ በሆኑት በተከበሩ ተማሪ አፈወርቅ ብርሃኔ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ከሞዴል ህፃናት ፓርላማ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች ከቋሚ ኮሚቴዎችና ከመድረኩ መልስ ተሰጥቶበት የ2014 ዓ.ም የሞዴል ህፃናት ፓርላማ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
    በመጨረሻም ሹመት የተካሄደ ሲሆን በዚሁ መሰረት ለሞዴል ህፃናት ፓርላማ ም/ፕሬዚዳንትነት የተከበሩ ተማሪ ፈትሂያ ጠይብ የተሾሙ ሲሆን ለሞዴል ህፃናት ፓርላማ የባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን የተሸሙት ደግሞ የተከበሩ ተማሪ ሚካኤል ደምመላሽ ሲሆኑ የሁለቱም ሹመት ከፀደቀ በኋላ ሹመታቸውን በተስፋ ቃለ-መሀላ ፈፅመዋል፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር የሞዴል ህፃናት ፓርላማ 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በዚሁ ተጠናቋል፡፡