የድሬደዋ መተዳደሪያ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 ለማሻሻል በተዘጋጀ ረቂቅ ላይ ውይይት ተደርጓል።
ድሬዳዋ ሐምሌ 23/1996 በወጣው አዋጅ ቁጥር 416/1996 እራሷን በራሷ እንድታስተዳድር መደረጉ ይታወሳል።ይሁን እንጂ በስራ ላይ ያለው ቻርተር በወቀቱ የነበሩ ችግሮችን በአንፃራዊነት ያስወገደ ቢሆንም በቻርተሩ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ድንጋጌዎች በአስተዳደሩ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማያመላክቱ፣በአወቃቀርና በአሰራር ላይ አንዳንድ ችግሮችን ያስከተሉ በመሆናቸው ችግሮችን በማስወገድ የአሰራርና የአደረጃጀት እንዲሁም ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ በሚያሰፍን ከወቅታዊ እድገትና ልማት አቅጣጫ ጋር በሚጣጣም መልኩ እንዲሻሻል ማድረግ ማስፈለጉ በመድረኩ ተገልጿል።
-በተለይም ቻርተሩ በአስተዳደሩ ያለውን የገጠር ክፍል ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ በአስተዳደር ጉዳይ ላይ ተፅህኖ እያሳደረ እንደሚገኝ፣ የአስተዳደሩን የስልጣን አካላት አደረጃጀት በማእከልና በቀበሌ ደረጃ ብቻ በመሆኑ እያንዳንዱን አካባቢ አሰተዳደር በማጠናከር የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጠናከር፣ የተሻለ የሃብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ ፣ በቻርተሩ አንቀጽ 12 ንዑስ ቁጥር 1 ላይ የተማለከተው የአስተዳደሩ ምክር ቤት ህግ የማውጣት ስልጣን የተገደበ መሆኑ የሚልቱን ጨምሮ ሌሎች ወቅታዊና የወደፊት የልማትና እድገት አቅጣጫን ባገናዘበ መልኩ በስራ ላይ ያለው አዋጅ ማሻሻያ እንዲደረግበት የቀረበው እረቂቅ እንደሚያስችል ተብራርቷል።
እረቂቁ ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በዋነኝነት ለረጅም አመታት የድሬደዋን እድገት ወደኋላ ሲጎትቱ የነበሩና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ሲገድቡ የነበሩ ማነቆዎችን ሊቀርፍ የሚችል መሆኑ ተንፀባርቋል።በተለይም አንዳንዶቹ ችግሮች በፖለቲካዊ ውሰኔ የተፈጠሩ በመሆናቸው አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ እርምት እንዲደረግባቸው መስራት እንደሚገባ ከተሳታፊዎች ተነስቷል።
10 ክፍሎች 79 አንቀጾች እና 194 ንዑስ አንቀጾች ያሉት ይህ የማሻሻያ እረቂቅ አዋጅ በቀጣይ በተለያዩ ውይይቶች ዳብሮ እንደሚፀድቅ ለማወቅ ተችሏል።
የድሬደዋን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ቻርተር ሊኖር እንደሚገባ ተገለፀ


