የክረምት በጎ ፍቃድ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ጊቢ ዉስጥ በዛሬው እለት ተከናወነ።

    መርሃግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የፓርቲው የልማታዊ ተቋማት እቅድ ዝ/ክ/ድ/ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡመር አህመድ፣ የአስተዳደሩ ቀይ መስቀል ማህበር እና ስካውት ክለብ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በእለቱ ከችግኝ ተከላዉ በተጨማራ አቅመ ደካማና የአካል ጉዳተኛ የሆነች የአንዲት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ጥገና የማስጀመር ስራ ተከናዉኑዋል ።