በአስተዳደራችን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርህ ግብር ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይቷል። ድሬዳዋ አስተዳደር አሁን እየጣለ ካለው ዝናብ ጋር ተያይዞ ለችግኝ ተከላ መርህ ግብር ምቹ በመሆኑ በአንድ ጀንበር 700 ሺህ ችግኞች የፊታችን እሁድ ነሀሴ 8/ 2014 በከፍተኛ የህብረተሰብ ታሳትፎ ለማከናወን የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቆ ፤ ለ38ቱም የገጠር ቀበሌና 9 የከተማ ቀበሌዎች የችግኝ ማጓጓዝ ስራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።