በድሬዳዋ አሰሊሶ ገጠር ቀበሌ የምክር ቤት አባላት ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረጉ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በትላንትናው እለት የተጀመረው የህዝብ ውክልና አወጣጥ የውይይት መድረክ በዛሬው እለትም በአሰሊሶ ገጠር ቀበሌ የአስተዳደሩ ምክር ቤት ተወካዮች የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዋች ዙሪያ የአካባቢውን ማህበረሰብ አወያይተዋል።
    በውይይቱ የተሳተፉ ተሳታፌዋችም በሰጡት አስተያየት በአካባቢው ያሉ ስረአጥ ወጣቶቾ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸውና ሴቶች በማህበር ተደራጀተው የሚሰሩበት እድል እንዲፈጠርላቸው እንዲሁም በአካባቢው ያለው የውሀ እጥረት እንዲቀረፍላቸው እና የመኪና መንገዶች በጎርፍ የተሸረሸሩ በመሆናቸው እንዲሰሩላቸው በውይይታቸው ላይ አንስተዋል።
    የውይይት መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የአሰሊሶ ተወካይ የተከበሩ አቶ ቡሌ መሀመድ እንደተናገሩት በአንደኛው ዙር የህዝብ ውይይት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ የውሀ ፣የመንገድ ፣የጤና ጣቢያ የፖሊስ ጣቢያና የመስኖ ውሀ ጥያቄዋች ከማህበረሰቡ መነሳታቸውን በመጠቆም ይህ የህዝብ ችግር ለመፍታት በምክር ቤት ደረጃ በመወያየት የትምህርት ቤት እና የመስኖ ውሀ የተጠናቀቁ ሲሆን በቀጣይ የቀሩ የልማት ስራዋችን በማከናወን የማህበረሰቡን ጥያቄዋች በቅደም ተከተል ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።
    ከዚህም በማስከተል የተከበሩ አቶ ቡሌ መሀመድ እንደገለፁት በዛሬው እለትም ከማህበረሰቡ የሚነሱ ጥያቄዋችን አፉጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመሆን ውጤታማ ስራ እንሰራለን ብለዋል።