በድጋፍ አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የተቋሙ ሥራ አስኪያጅ አቶ እውነቱ ወርቅነህ የት/ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አዶሽ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ርዕሳነ መምህራን፣ ፣ ወላጆች ና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ ስራ አስኪያጅ ተቋሙ ለበጎ አድራጎት ስራ የሚዉል በጥቅሉ 180,000 ብር መመደቡን ገልጸዉ ከዚህ ዉስጥ 60,000 ብር የትምህርት ግብአት የመግዛት አቅም ለሌላቸዉ ተማሪዎች ድጋፍ የተያዘመሆኑን አብራርተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አቡበከር አዶሽ በበኩላቸዉ ለተደረገው የድጋፍ ስጦታ በራሳቸውና በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው ሌሎችም ተቋማት ይህንን አርዓያነት ያለው ተግባር ሊከተሉ ይገባል ብለዋል ማንም ህጻን በትምህርት መርጃ ግብአት እጦት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ዉጪ እንዳይሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት አለበት ሲሉ መልዕክታቸዉን አሰተላልፈዋል።
በመድረኩም የ ዳዊት እና አሰገደች የአረጋዊያን መርጃ ድርጅቶች
ለያንዳንዳቸዉ የ60,000 ብር ድጋፍ በኮርፖሬሽኑ ተበርክቶላቸዋል ።
ዘገባዉን የድሬዳዋ አሰተዳደር ት/ቢሮ ኮሙኒኬሽን ነዉ ያደረሰን


