ከነሃሴ 16/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ “በጎነት ለጤናችን” የነፃ ምርመራና ህክምና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘመቻ ወቅት የተጠናከረ የጤና አጠባበቅ ትምህርት፣የደም ግፊት ምርመራና ህክምና ፣የደም ውስጥ ስኳር ምርመራና ህክምና እና ሌሎችም ያለምንም ክፍያ የሚሰጡ ይሆናል።
በአስተዳደራችን በዋናነት 3 ግዜያዊ የነፃ ምርመራና ህክምና ጣቢያዎች የሚቋቋሙ ሲሆን የታሰቡት ቦታዎችም
1. ምድር ባቡር አደባባይ
2. ኮኔል ድልድይ
3. ሳቢያን ማደያ አከባቢዎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም በአስተዳደራችን ከተመረጡና እድሳት ከሚያስፈልጋቸው ቤቶች ውስጥ አንድ ቤት የማደስና መሰረታዊ የቤት ቁሳቁሶችን የሟሟላት እንዲሁም ለ100 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ማዕድ የማጋራት ስራ በጤና ቢሮና በስሩ ባሉ ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት ባለሞያዎችና ሰራተኞ ች በተሰበሰበ ገንዘብ ይከናወናል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ


