የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ሳይቶች ላይ ሕንጻዎችን ለመገንባት የሚያስችለውን የቅድመ-ዝግጅት ሥራ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያው ዙር ከሚገነባቸው የግንበታ ሳይቶች መካከል በሆነው ኢሚግሬሽን ሳይት ለሚገነባው ዘመናዊ ሕንጻ የግንባታ መሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ የግንባታ ሒደቱን አስጀምሯል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ የሚገነባቸውን ግንባታዎችንም በተመለከተ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ከድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር ፣የም/ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ የአሰተዳደሩ ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ፣የአሰተዳደሩ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ…


