“ኢሬቻን የሚያከብር ሰው ቂምን በመፀየፍ ሰላም፣ አንድነት፣ ኅብረትና ወንድማማችነትን መርሁ ያደርጋል” የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ።

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለ2017 ዓ.ም ኢሬቻ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ኢሬቻ የሰላም፣ የዕርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ነው ብለዋል።

እንደ ኢሬቻ ባለ ብርቅዬ እሴቶቻችንና ባህላችን ዙሪያ ተሰባስበን፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ የሚያደናቅፉን ዕንቅፋቶችን ሁሉ በመንቀል ዛሬ ላይ ሆነን ነገን የበለጠ ብሩህ ለማድረግ ጠንክረን ልንሠራ ይገባል።

የኢሬቻ በዓል አንድነታችንን የሚያጠናክር መሣሪያ አድርገን በመያዝ ከውጭና ከውስጥ የሚገጥሙ መሰናክሎችን በማለፍ የሀገራችንን ብልፅግና ለማሳካት እጅ ለእጅ በመያያዝ መረባረብ ይገባል።

ዘመኑ ሰላምና ዕርቅ የሚሰፍንበት ስኬትን የምንጎናፀፍበት፣ ዘርተን የምናጭድበት፣ የበረከትና የጥጋብ እንዲሆን በመመኘት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መልካም የኢሬቻ በዓል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *