ጊዜው የሚጠይቀውን አሰራር በመከተል ፈጣንና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማህበረሰቡ የማድረስ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም በኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ የተመዘገበውን ውጤታማ አፈፃፀም በ2017 በጀት ዓመት በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል ለኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄደ::

በመርሀ-ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በ2016 ዓ.ም በርብርብና በቅንጅት በመሆን በሚዲያና በኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው፤ ለዚህም አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

አቶ ብሩክ አያይዘውም ጊዜው የሚጠይቀውን አሰራር በመከተል ፈጣንና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማህበረሰቡ የማድረስ ስራዎች በ 2016 ዓ.ም መሰራታቸውን ገልጸው ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም በ2017 ዓ.ም በ2016 ዓ.ም የተጀመሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበትና ክፍተት የታየባቸው ቦታዎች ላይም በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ብሩክ አመላክተዋል፡፡

እውቅናና ሽልማት የተበረከተላቸው የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በበኩላቸው የተበረከተው ሽልማትና እውቅና ለቀጣይ ጊዜም በርትቶ ለመስራት የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቁመው፤ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ፡-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *