ማህበሩ ለድሬዳዋ ልማት ማህበርም የአንድ መቶ አስር ሺ ብር ድጋፍ ያበረከተ ሲሆን፤ ድጋፉንም የማህበሩ አመራርና አባላት ለድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አስረክበዋል::
በርክክብ መርሀ-ግብሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የአሸዋ ህዳሴ ማህበር ደርዘን ተራ ነጋዴዎች ንብረታቸውን በእሳት አደጋው ላጡ ወገኖች ያበረከቱት ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ማህበሩ ድሬዳዋን ለማሳደግም ለድሬዳዋ ልማት ማህበር ላበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ድጋፉን ያበረከትነው ንብረታቸው በአደጋው የወደመባቸውን ወገኖች ለመደገፍና ከጎናቸው መሆናችንን ለማሳየት ነው ሲሉ የተናገሩት ደግሞ ድጋፉን ያስረከቡት የማህበሩ አባላትና አመራሮች ናቸው::
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አብይ ሽመልስ


