የድሬዳዋ አስተዳደር ለሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሽከርካሪ ስጦታ አበረከተ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ለአስተዳደሩ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መገልገያ የሚሆን የመኪና ስጦታ አበርክቷል።

በመርሀ-ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የመኪናውን ቁልፍ ለድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ሼህ ኢብራሂም ኢማም እንዲሁም ለድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ሊቀብርሀናት ቀለመወርቅ ቢምረው አስረክበዋል::

ክቡር ከንቲባ ከድር የድሬዳዋ አስተዳደር የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ማህበረሰቡን በጎ ነገር በማስተማር እንዲሁም በሰላም ግንባታ ላይ ከአስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ለዚህም አመስግነዋል፡፡

ከንቲባ ከድር አያይዘውም ይህ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአስተዳደሩን ከጎን በመሆን የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ በሰዓት ለመገኘት ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት ችግር ይገጥማቸው እንደነበረ ጠቅሰው ይህንን ችግር ለመፍታትም አስተዳደሩ የመኪና ስጦታ ማበርከቱን ገልፀዋል::

ከዚህ ቀደም በትራንስፖርት ይቸገሩ እንደነበረና ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድም ባጃጅን/ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪን/ ሲጠቀሙ እንደነበረ የገለፁት ደግሞ የጉባኤው ምክትል ሰብሳቢ ሊቀ ብርሀናት ቀለመ ወርቅ ቢምረውና የድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ፓስተር ሚኪያስ ታዬ ናቸው፡፡ በዚህም አስተዳደሩ ያለብንን ችግር ተመልክቶ ላበረከተው ድጋፍ ተደስተናል በማለት ስሜታቸውን ያጋሩም ሲሆን ፤ ለአስተዳደሩም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ፤-አብይ ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *