በአስተዳደሩ ለሚንቀሳቀሱ የመንግስት ተሽከርካሪ ሹፌሮች በተሻሻለው የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

አሽከርካሪዎች መሰል መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ሶስተኛ ቀኑን በያዘውና በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችን በተሻሻለው የመንገድ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ላይ የግንዛቤ ለማስጨበጫ የተዘጋጀው መድረክ ማጠናቀቂያውን አድርጓል። በመድረኩ የደንቡ መሻሻል ባስፈለገባቸው ነጥቦችና በደንቡ የተካተቱ የጥፋት እርከኖች ላይ ለመንግስት ተሽከርካሪ ሹፌሮች ማብራሪያ ሰቷል። የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግም አሽከርካሪዎች ባነሱት ሀሳብ ተሽከርካሪዎቻችን በወቅቱ ሰርቪስ አይደረጉም ብልሽት ሲገጥማቸው ወቅታዊ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሀይማኖቶች ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚካሄደውን የሰላም ኮንፍረንስን አስመልክቶ ለፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ሰጠ

በዚህም በመድረኩ ከሰባቱም የእምነት ተቋማት የተውጣጡ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል። በኦረንቴሽኑ ወቅት ያነጋገርናቸው ወጣቶችም የሀይማኖት ተቋማት ስለ አንድነት፣ ስለ ሰላም እና ህብረት ሁሌም እያስተማሩ እንደሚገኙ አንስተው፤ እኛ ወጣቶችም የድሬዳዋን ሰላምና አብሮነት እንደ ሁሌውም አጠናክረን የማስቀጠል ሀላፊነት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ድሬዳዋ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም ኮንፍረንስ ሊዘጋጅባት መሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተሳታፊዎቹ አያይዘው ገልፀዋል። በመጨረሻም ወጣቶቹ ኮንፍረንሱ…

Read More

የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን እና ከንቲባዎች በ19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላይ ለመታደም አርባምንጭ ከተማ ገቡ

የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል። እንግዶቹ አርባምንጭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የጋሞ አባቶች ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል። EBC

Read More

የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ

“ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል ” በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም ለ 21 ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ 20 ኛ ጊዜ የአለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች የሚከበር ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በዛሬው እለት የተማሪዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ጥያቄና መልስ ውድድር አካሂደዋል ። ሙስና በተለይም የራስ ያልሆነን ነገር በአቋራጭ እና በጉልበት…

Read More

በሀገር አቀፍ ደረጃ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የሰላም ኮንፍረንስ በድሬዳዋ አስተዳደር ሊካሄድ ነው

“ሀይማኖቶች ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር እንደ ሀገር የመጀመሪያ የሆነ የሰላም ኮንፍረንስ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስታዲየም ሊካሄድ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። የኮንፍረንሱ ዋነኛ አላማም የድሬዳዋ ህዝብ በፍቅር፣ በአብሮነትና በአንድነት ሰላሙን አስጠብቆ እየኖረ በመሆኑ ለመላው የድሬዳዋ ህዝብና ለከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ለሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምስጋናና…

Read More

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባምንጭ የተደረገላቸው አቀባበል

19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ነገ ለማክበር የተዘጋጀችው እንግዳ ተቀባይዋ የአርባ ምንጭ ከተማ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ለከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርጋለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

Read More

“ደቡብ ኢትዮጵያን መጎብኘት እና እንደ አርባምንጭ ያሉ ከተሞችን እድገት መመልከት ሁልጊዜም አስደሳች ነው!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እንደ ሀገር የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ለከተሞችም ሆነ ለገጠር አካባቢዎች ፈተና ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በመጎብኘት ላይ እንዳለነው አይነት የሙዝ ልማት ሥራዎችን በገጠር አካባቢዎች በማሳዎች ላይ የኩታ ገጠም እርሻ አሰራረን ጀምረናል ብለዋል። እነዚህን ጥረቶች የሚደግፈው የሌማት ትሩፋት ሥራ በየአርሶአርብቶአደሩ ቤት የእንቁላል ምርትን ከአሳ እና ከብት ርባታ ብሎም ንብ ማነብ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዳዳ ገጠር ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የድህረ ተከላ እና የደን እንክብካቤ ስራ ተካሄደ።

#DGC ህዳር 28/2017 የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዳዳ ገጠር ቀበሌ ላይ መምህራን ፣ ተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ያሳተፈ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ድህረ እንክብካቤ ስራዎችን አከናወኑ። የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የደን ልማት ቡድን መሪ አቶ ማሙሽ ዘውዱ በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት እንደገለፁት ችግኞችን ከተከሉ በኋላ በመኮትኮት ፣ ውሃ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የፀረ ሙስናን ቀን አስመልክቶ የፖናል ውይይት አካሄዱ

በአለም አቀፍ ለ21 በሀገራችን ለ20 ጊዜ ”ከወጣቶች ጋር በመተባበር ሙስናን መከላከል፤ የነገ ስብዕናን ለመቅረፅ”በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የፀረ ሙስናን ቀን አስስመልክቶ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አመራር እና ባለሙያዋች የፖናል ውይይት አካሄዱ። የመወያያ ሰነዱ በቢሮው የለውጥ ስራዋች እና የመልካም አስተዳደዴር ዳይሬክቶሬት ዴይሬክተር አቶ ተስፉሚካኤል ኤድሞያስ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በተሳታፊዋችም የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነሰሰተዋል።

Read More