የታንዛንያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ለማረግ ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል
ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን ማክሰኞ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል። ብሄራዊ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ እንዲሁም በካቢኔ አባላትና በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።


