ይህ ዘመን በታሪካችን ውስጥ በጉልህ የሚነሳ ነው፡- ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይህ ዘመን በታሪካችን ውስጥ በጉልህ የሚነሳ ነው ሲሉ ገልጸዋል። እኛ ኢትዮጵያውያን ለበርካታ ዘመናት ስንቆጭባቸው የነበሩትን ታላላቅ ፕሮጀክቶች ያስመረቅንበት ልዩ ዓመት አሳልፈናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ የትውልዱ ቁጭት የነበረውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አጠናቀን ታሪክ ሰርተናል ብለዋል። በመስከረም ወር…

Read More

የዲፕሎማሲያችን ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው፦ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ

ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዲፕሎማሲያችን መሰረታዊ ማዕከል እና ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ስትራቴጂያዊ ምርጫ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለመሸጋገር አስችሎናል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል፤ በዛው…

Read More

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በሁለቱ ም/ቤቶች መክፈቻ ሥነ ሥረዓት ላይ ማቅረብ ጀምረዋል

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌደራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ማቅረብ ጀምረዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Read More

የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ – ሥርዓት ተጀመረ

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ – ሥርዓት ተጀምሯል። የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

Read More

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ተመረቀ

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በይፋ ተመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢኒያም ኤሮን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ…

Read More

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ነገ ይካሄዳል::

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ይካሄዳል። የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን÷ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት…

Read More

የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በስኬት መጠናቀቁን አባ ገዳ ጎበና ሆላ አስታወቁ::

የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ፥ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ የ2018 ዓ.ም የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በስኬት መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅዖ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ::

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የሆረ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከብሯል። በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ታድመዋል።

Read More