የዲሞክራሲ ጉዟችን ማሳያ የሆነ የዘንድሮው ምርጫ ካለፈው የተሻለና አካታች ይሆናል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ፣ የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ሁሉንም ወገን ያካተተ እንዲሆን መንግሥት በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ምርጫውን በሚመለከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸው መልስ “በውጤት እንየው” የሚል መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሂደቱ በሰላም እንደሚከናወንና በምርጫው የሚሳተፉ የፖለቲካ ኃይሎችም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል። በተለይም ከምርጫው በኋላ የሚመሰረተው ፓርላማ…


