በድሬዳዋ አስተዳደር ከስደት ተመላሽ ወገኖችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ::
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ኢሮፒያን ዩኒየን፣ ከእንግሊዝና ከስዊድን ኤንባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ፅህፈት ቤት የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም አቅምን የማሳደግ ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር ምክክር አድርጓል። በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ስደተኛ እና ከስደት ተመላሽ ወገኞች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ እንዲሁም ስደትን በዘላቂነት ከመከላከል አኳያ በአስተዳደሩ…


