ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና ክብርት አዳነች አቤቤን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የተካተቱበት ልዑክ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል።


