“በወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል” – የወረዳ 09 ነዋሪዎች
በድሬዳዋ ወረዳ 09 እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በመንገድ መጣበብ ምክንያት እግረኛና ተሽከርካሪ እየተጋፋፋ የሚሄድበትን ሁኔታ በመቀየር መንገዶች እንዲሰፉ አድርጓል ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ አያይዘውም ከኮሪደር ልማቱ በፊት በአካባቢው በስፋት ያረጁ፣ የሸራና የቆርቆሮ ቤቶች ይገኙ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓት ግን ያረጁ ቤቶች ውበት ባላው እና በዘመናዊ መልኩ በአዲስ ተሻሽለው እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ለአካባቢ…


