“ኢትዮጵያ ክትባት ማምረት አትችልም” የሚለውን ምልከታ የቀየረው የምርምር ማዕከል
ኢትዮጵያ በመድኃኒትና በክትባት ምርት ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ግዙፍ የምርምር ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማዕከሉን በመረቁበት ወቅት፥ ከዚህ ቀደም ይህን መሰል መሰረተ ልማት ባለመኖሩ “ኢትዮጵያ መድኃኒትና ክትባት ማምረት አትችልም” በሚል የምናቀርበውን የአጋርነት ጥያቄ ብዙዎች ሳይቀበሉት ቀርተዋል ብለዋል። የዚህ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መገንባት ያንን…


