ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሁለተኛው ቀኑን ከያዘው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን፣ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፣ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።


