የፈጠራ ባለሞያዎችን ሥራ በማበረታታት ጠቃሚ የሆኑ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ውጤቶችን ለማጎልበት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የኤኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ክበባት አመራርና ሱፐርቫይዘሮች የፈጠራ ስራን ባህል ለማጎልበት ስራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል:: በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀዲ መሐመድ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁሉለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ እንደሆነ አውስተው ዘርፉ ለድሬዳዋ እድገት ሊያበረክት…


