በድሬደዋ ከተማ ለሚንቀሳቀሱ 200 ለሚሆኑ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የሌሊት ታክሲ አገልግሎት ፍቃድ ተሰጠ፡፡
ተሽከርካሪዎቹ የአገልግሎት መስጫ መለያ ቁጥር በመውሰድ ወደ ስራ እየገቡ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡ የትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ቁጥራቸው ከ10ሺ የሚልቁ የታክሲ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ የህዝብና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አደረጃጀት ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ነጋ እንደሚናገሩት እኝህን ተሽከርካሪዎች በአግባቡ ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጡ በመቆጣጠር ረገድ የስምሪት ባለሙያውም ሆነ…


