ስድስት ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የደቻቱ ደረቅ አሸዋ ወንዝ ተፋሰስ የተቀናጀ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ጥናት እየተደረገ ይገኛል።
የፕሮጀክቱ የቤዝ ላይንና የዲዛይን ጥናት ለድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቂያ መድረክ በሐረር ከተማ ራስ ሆቴል ተካሂዷል። በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪኃጅ ፅ/ቤት UIIDP /የከተማ የተቀናጀ ተቋማዊ ልማት ፕሮግራም/ ስድስት ሚሊየን ብር በሚጠጋ ድጋፍ በሐሮማያ ዩንቨርሲቲ እየተደረገ የሚገኝው ጥናቱ የአስተዳደሩን የቀጣይ መቶና ሁለት መቶ አመታት ሁኔታ ትንበያ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ በመስተዋወቂያ መድረኩ…


