April 2021
6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ መራጩ ህዘብ ተገቢውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እና የዜጎችን ተሳትፎ በምርጫው ላይ እንዲኖር በበጎ ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ያለ ዜጎች ተሳትፎ እውነተኛ ዴሞክራሲና፣ ሕገ መንግስቱን እውን ለማረግ እንደማይቻል ሁሉ ከቅርብ ወራት በኋላ የሚካሄደውን 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተሳትፎ የዳበረ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በእንደዚህ ዓይነቶቹ ስልጠናዎች አማካኝነት ዜጎችን ማስተማር የምርጫው ውጤት ግልጽና በህዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲሆን፡፡ የስልጠናውን ያዘጋጀው ምስራቃዊ የዕድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር ከINITIATIVE AFRICA በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ 6ተኛው ዙር አገር…
በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን በተሻለ መልኩ ለመስራት ጠንካራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ::
በድሬዳዋ አስተዳደር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 21 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በህብረተሰቡ ተሳትፎ ኦጀንሲ ኃላፊነትና በዘጠኙም የከተማ ቀበሌዎች ቅንጅት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ የልማት ስራዎች በውጤት ለማጠናቀቅም መንግስት ከሚመድበው በጀት በዘለለ ከህብረሰተቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በዓይነት ድጋፍ እንዲደረግ ይጠበቃል፡፡ ይህንን መሰረት ባደረገ መልኩ በቀበሌ 05 አስተዳደር በህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ሲቀርብ የነበረው ቀርሳ ተራ የገበያ ማዕከል አካባቢ የተገነባው…
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች እራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ከመጠበቅ ባለፈ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሽታ በድሬዳዋ አስተዳደር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል ፡፡ በሽታው በሀገራችን ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በድሬዳዋ አስተዳደር 32 ሺህ 209 ለሚሆኑ ሰዎች የናሙና ምርመራ በማድረግ 3 ሺህ 718 የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ድረስም ከበሽታው ጋር ተያይዞ በከተማዋ የ 45 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በሀገር አቀፍ ደረጃ…
ለአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የታዳጊ ህፃናት የሰላም ዕውቀት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ::
በድሬደዋ አስተዳደር የምስራቅ ጀግኖች ት/ቤት ተማሪዎች በሀገራቀፍ የመጀመሪያው የሰላም ቀን ባከበሩበት ስነስርዓት ላይ የተገኙት የድሬ ደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ባደረጉት ንግግር ለአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የታዳጊ ህፃናት የሰላም ዕውቀት ከፊተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በየትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎቻችን ሰላምና አብሮነትን ፣ መብትና እና ግዴታን በአግባቡ እንዲረዱ ለማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን የሰላም እና የአብሮነት…
በነገው ዕለት በአስተዳደራችን የሚጀመረውን የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን ዙሪያ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር አስተናጋጅነት የሚካሄደው 4ኛ ዙር የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጫዋታዎች ከነገ መጋቢት 29/2013ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ሳምንታት ይካሄዳል፡፡ ይህንን እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኩሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡ በድሬዳዋ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለማዘጋጀትና ጨዋታን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአስተዳደሩ…
የደቻቱ ወንዝ ለልማት በማዋል ድሬዳዋን ማልማት ይኖርብናል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈጡም ሙስጠፉ። ስድስት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የደቻቱ ደረቅ አሸዋ ወንዝ ተፋሰስ የተቀናጀ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ ኢኒቬቲቭ የፕሮጀክት ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ የቤዝ ላይንና የዲዛይ ጥናት ለድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የደቻቱ ወንዝ…
7ኛው የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን መርሀግብር ድሬደዋ ላይ በተለያዩ መርሀ ግብሮች በድምቀት ተከብሯል፡፡
አሽከርካሪዎችም ሆነ ተሳፋሪዎች ማስክን ባግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው በመርሀግብሩ ተጠቁሟል፡፡ ወር በገባ የመጨረሻው እሁድ ሚከበረው የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችና የእግረኞች ቀን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ ድሬደዋ ላይ ተከብሯል፡፡ በስነ_ስርዕቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት መርሀግብሩ ማህበረሰቡ አማራጭ የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችንና የእግር ጉዞ ባህልን እንዲያጎለብት ገንዛቤን በመፍጠር…
በአስተዳደሩ ከሰሞኑ በተደረገው የመንገድ ለውጥ …….
ማህበረሰቡ በመንገድ ለውጡ ላይ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የአስተዳደሩ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ ጣሀ ፤የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ፤ በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ፤ እንደሁም በድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ይሄነው ሽፈራው ጨምሮ ሌሎች ሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በስፍራው ተገኝተው የመንገድ…


