ከንቲባ ከድር ጁሀር በምክር ቤት ያደረጉት ንግግር
የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ለዛሬ የመንግስት ምስረታ በነፃ ፍቃዳችሁ ይሁንታችሁን የሰጣችሁ የድሬዳዋ አስተዳደር መላው ነዋሪዎች ክብራትና ክቡራን:- በቅድሚያ የሉዓላዊነት መገለጫ በሆነው በተከበረው የአስተዳደሩ ምክር ቤት ፊት በመገኘቴ እንዲሁም እትብቴ በተቀበረባት፣ በተማርኩባትና፣ በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ባገለገልኩባት የትውልድ ከተማዬ ትልቅ ሃላፊነትና አደራን በመቀበል፣ ድሬዳዋችንን እንድመራ በከንቲባነት በመሰየሜ የተሰማኝን ታላቅ ክብር እና ደስታ ስገልጽ ከልብ በመነጨ ምስጋና ነው፡፡ በሀገራችን ታሪክ…


