በፌዴራል ደረጃ በሕዝብ የተመረጠውና በአዲስ መልክ የተዋቀረው መንግሥት ይመሠረታል::
በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት በሕዝብ የተመረጠውና እንደገና የተዋቀረው አዲስ መንግሥት ዛሬ በፌዴራል ደረጃ ይመሠረታል። የኢፌዲሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ ዛሬ እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቋል፡፡ የምክር ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ላይ ተገኝተው…


