በድሬዳዋ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ነዉ
በድሬዳዋ አስተዳደር “እናት እና አባታችንን ለመደገፍ እንሩጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ታዋቂ አትሌቶች እና በርካታ ህብረተሰብ የተሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ነዉ። ዳዊት አረጋውያን መርጃ ማዕከል ከወጣቶች ና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈትያ አደን…


