ምክር ቤቱ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ አዋጅ አጸደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ የንብረት ማስመለስ አዋጅን አጽቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው። የቋሚ ኮሚቴው…


