በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራቶች ይኖሩናል፦ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ በሚቀጥሉት ወራት ለኢትዮጵያ ህዝብ ብስራቶች ይኖሩታል ሲሉ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። “ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተጓዝነው የብልፅግና ጉዞ ምዕራፍ አንድ ከጥልቅ እንቅልፍ፣ ከብዙ ዕዳ መንቃት የጀመርንበት የመነሳት ዘመን ነበር” ብለዋል በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው። በዚህ ምዕራፍ የታሰረ ይፈታ፣ የተሰደደ ይመለስ፣ ያኮረፈ ይታረቅ፣ ከመከላከያም ሆነ ከዩኒቨርሲቲ የተባረረ ይመለስ፣ በእምነት ተቋማት የተከፋፈለ…


