“የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ ኢትዮጵያ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ናት” ሲሉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ ዕድል እንዳቀረበ አፅንኦት ሰጥተው ማንሣታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው…


