የጳጉሜ ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ስያሜዎች ታስበው ይውላሉ፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የ2017 ዓ.ም አምስቱ የጳጉሜ ቀናት ስያሜዎችን እና የአከባበር ሁኔታ አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ የጳጉሜ ቀናት መታሰብ ዜጎች ለአዲስ ዓመት የግላቸውን መሻት እውን ለማድረግ ሲያቅዱ የመንግስት መነሳሳቶች፣ እቅድ እና አቅጣጫዎችን በእቅዳቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተጠናቀቀው የ2017 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ፣ የኮሪደር ልማት፣…


