በፖለቲካ ሉኣላዊነት የተቀናጀነውን ድል በኢኮኖሚውም መድገም አለብን ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒሥቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ገለፁ።
በሥራና ክሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 08 እና ዐ4 የተሰሩ የከተማ ምግብ ዋስትና ሥራዎችን ገምግመዋል። ሚኒስቴር ድኤታው በፖለቲካ ሉኣላዊነት የተቀናጀነውን ድል በኢኮኖሚውም መድገም አለብን ሲሉ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ቀና ብላ እንድትሄድ ለማስቻል በሁሉም ዘርፍ ፍሬያማ ሥራ መሰራት አለበት ብለዋል። በተለይ በሴፍቲኔት ተረጂ የሆኑትን ግለሰቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማስገባት…


