የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ ስራዎችን በፍጥነት፣ በጥራትና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
በሀገር አቀፍ ደረጃ አምራች ኢንደስትሪውን ለመደገፍና ለማበረታታት መንግስት ባዘጋጀው የአምራች ኢንደስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ በዛሬው ዕለት በዘርፉ ከሚገኙ ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ስራዎችን በመደጋገፍና ተቀናጅቶ መስራት የአምራች ኢንደስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ምክትል ከንቲባ አያይዘውም ከለውጡ አመታት ወዲህ…


