ብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ በዋሂል ክላስተር ለሰባተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ተሳታፊ ዕጩዎቹን ለህዝብ አስተዋወቀ
ዕጩዎችን በመወከል በዋሂል ክላስተር ለተገኙ ታዳሚዎች ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባልና የአስተዳደሩ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነጻ ፣ ገለልተኛ እና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው ብልጽግና በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ በዋሂል ክላስተር የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ ተመልምለው የቀረቡ ዕጩዎች ቀደምሲል በምርጫ ቦርድ ከመመዝገባቸው…


