ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በክቡር ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በሀይማኖት አባቶች እና በድሬዳዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል::
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዶ/ር ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ እና ከልኡካን ቡድናቸው ጋር ወደ ድሬዳዋ የገቡት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሲሆን በከተማው የተከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የሚጎበኙ ይሆናል። በሶማሌ ክልል በ”ገበታ ለትውልድ” መርሃ-ግብር የተገነባውን ግዙፍ የሸበሌ ሪዞርትን እንዲሁም አይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫን ከጥቂት ሰዓታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተዋል።


