ለቀጣይ የሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት ስኬታማነት እርስ በእርስ ተሞክሮዎችን መለዋወጥና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ::
በካናዳ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በሶስቱ ሰብሰሀራ አፍሪካ ከተሞች ማለትም በጁሀንስበርግ፣ በኪጋሊና በድሬዳዋ እየተተገበረ የሚገኘው የሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት የስራ ሂደት ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ። በዚህም በፕሮጀክቱ ትግበራ በድሬዳዋ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅእኖ መቋቋም የሚያስችሉና የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን የሚቀንሱ ስራዎች መሰራታቸውን በተጨማሪም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠቱ ተገልጿል። በፕሮጀክቱ ከ7 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ የተጠቆመ…


