የአብሮነት እሴቶችን ይበልጥ በማስቀጠል ለዘላቂ ሰላም መስፈን ሁሉም አካል የድርሻዉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
በሃይማኖት መከባበር እና መቻቻል ዙረያ የውይይትና ምክክር መድረክ ተካሄዷል:: በእምነት አባቶች ፀሎትና ምርቃት በተጀመረዉ የዉይይትና ምክክር መድረክ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የድ/ዳ/አስ/ፍ/ፀ/ህ/ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ የአብሮነት እሴቶችን በማሰቀጠል ግጭቶችን በመፀየፍና በማስቀረት ሁል ግዜም ለዘላቂ ሰላም መስፈን ይበልጥ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ለእዚህም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ወሳኝ ስለመሆኑ ነዉ የተናገሩት:: ከቤተሰብ ጀምሮ…


