የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባህል እና ቱሪዝም ፅ/ቤት ፣ የድሬ ብድር እና ቁጠባ ተቋምን የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ምልከታውን አድርጓል ።

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለ4ኛ ቀን የመስክ ምልከታውን ቀጥሎ ያካሄደ ሲሆን በዛሬው እለት የድሬደዋ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ፅ/ቤት እና በቱሪዝም ሚኒስቴር ቅንጅት እየተሰራ ያለ ላንድ ማርክ ፕሮጀክት አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ምልከታ ካደረገ በኋላ ከዚራ የሚገኘውን የቅዱስ ሚናስ ቤተ ፀሎት፣ የአርመን ሀዋሪያዊት ቤተክርስቲያን እና ለገሀሬ ገንደ- ገበሬ የሚገኘውን…

Read More

የድሬዳዋ አሰተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

በመጀመሪያ ለመላዉ የአሰተዳደራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሠላም የጤና እና የፍቅር እንድሆንልን እመኛለሁ በአሰተዳደራችን ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር እንዲያከብር በዚህ አጋጣሚ ለመላዉ የእምነቱ ተከታዮች መልዕክቴን ለማሰተላለፍ እወዳለሁ። በዓሉን የሚያከብረዉ ህዝበ ክርስትያኑን ጨምሮ መላው የአሰተዳደራችን ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣…

Read More

የምወዳችሁና የማከብራችሁ ክርስቲያን ወገኖቼ፤ የገናን በዓል #እንዴት ለማክበር አሰባችሁ❓

ሁሌም በዓል ሲደርስ ከቤተሰብና ከወዳጅ ዘመድ ጋር በህብረት ማክበር የብዙዎቻችን ፍላጎትና ደስታ ነው። ልክ እንደ እኛ ይሄ ፍላጎት ኖሯቸው… በበዓል ቀን ህዝባቸውን ለማገልገል ሲሉ በፀጥታና ደህንነት፣ በህክምና፣ በትራንስፖርት፣ በሚዲያ እና ሌሎች ስራዎች ላይ የሚያሳልፉ ወገኖቻችን በርካታ ናቸው። በአቅማችን የበዓል ስጦታ ይዘን፤ ብቻቸውን እንዳልሆኑ፣ ለአገልግሎታቸውም ልዩ ክብርና ምስጋና እንዳለን ብንገልፅላቸው፤ የሚያገኙት ደስታ ልዩ እንደሚሆን አምናለሁ። ለሰላምና…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ጎበኙ

በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ጎበኙ። በድሬዳዋ አስተዳደር በ 2015 በጀት አመት በፌደራል መንግስት ከሚሰሩት የልማት ፕሮጀክቶች ውጪ ከ 170 በላይ የሚሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ለመስራት የታቀዱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 5 ግዙፍ የልማት ፕሮክቶችን በመምረጥ እነዚህም የልማት ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ ከመገምገም ባለፈ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያይዞ ያሉትን የካሳ ክፍያ ጥያቄዎች በተጨባጭ ለማየትና…

Read More

ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በተለያዩ መርሀ ግብሮች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬደዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በየዓመቱ ህዳር 11 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በዓለም ደረጃ ለ33ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ ’’ ምቹ እና ሰላማዊ ኢትዮጵያ ለሁሉም ህጻናት!’’ በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች እንደሚከበር የድሬደዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሟላት አቅም ለሌላቸው የአስተዳዳሩ ተማሪዎች የሚውል የደብተር እና ስክሪብቶ ድጋፍ አደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እየሰራ ከሚገኘው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ጎንለጎን እንደ ተቋም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትም የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ነፈይገኛል። ቢሮው እየተወጣቸው ማህበራዊ ኃላፊነቶች መካከል አነዱ በቅርቡ በ01 ቀበሌ የተረከበው እና ግንባታውን በማጠናቀቅ ላይ ነፈየሚገኘው የወ/ሮ አሁዶ የመኖሪያ ቤት አንዱ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ…

Read More

በደም ተሳስረው ለዘመናት አብረው የኖሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች የሃይማኖት፣ የቋንቋና የባህል ልዩነቶቻቸውን አክብረው ዛሬም በፍቅርና በመከባበር እየኖሩ ይገኛሉ።

አክብረው በአንድነት ያቆዩዋቸውን እሴቶቻቸውን አጠናክሮ መቀጠልም ሰላማዊ የሆነ ማህበራዊ መስተጋብርና ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ይፈጥራል። ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ሀብት እና የአንድነት መሰረት መሆናቸው ብዙዎችን የሚያስማማ ጉዳይ ነው። እነዚህን የሀገር ሀብቶች ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ሳይበረዝ ለትውልድ ማስተላለፍ ቀጣይዋን ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ለመገንባት አበርክቶው ከፍ ያለ ነው። ሁሉም ሐይማኖት የሚያስተምሯቸው እና የሚያጎናጽፋቸውን መቻቻልን፣…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለ120 ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለአንድ መቶ ሀያ ተማሪዎች ብዕር፣ ደብተር፣ እንዲሁም ዩኒፎርም አሰፍቶ ለትምህርት ቢሮ አስረክቧል፡፡ በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር በማድረግ ድጋፉን የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ ሙክታር ናቸው፡፡ አቶ አብዲ የቢሮ ሰራተኛው ተርፎት ሳይሆን ካለው ላይ ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን…

Read More

|በድሬዳዋ ከተማ በ5 ቢሊዮን ብር ወጭ በሀገር ውስጥ ባለሀብት ሙሉ ለሙሉ የሚለማ የኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ በኢትዮጵያ የመጀመሪው በሀገር ውስጥ ባለሀብት የሚለማ ብቸኛው ፓርክ እንደሆነ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ‘ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ’ ከተሰኘ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በድሬዳዋ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ እና የ’ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ’ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ታደሰ አድማሱ ተፈራርመዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ116 ሄክታር መሬት ላይ…

Read More