የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀመጠ

የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከዚህ በላይ ለመሄድ እንዳይችል አንዱ ዕንቅፋት በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት የተፈጠሩ ትሥሥሮች ያስከተሏቸው አካባቢያዊ ግጭቶች መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በስብሰባው ገምግሟል። እነዚህን ግጭቶች በመፍታት የብልፅግና ጉዞን ይበልጥ ለማፋጠንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል አግባብ የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በስብሰባው አቅጣጫ ተቀምጧል። በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን…

Read More

የባሕር በር ለማግኘት የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ አሳለፈ

ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል። ኢትዮጵያ እያደገ ከሚሄደው የሕዝብ ብዛቷና ኢኮኖሚዋ ጋር የሚመጣጠን የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ፓርቲው ካስቀመጠው አቅጣጫ በመነሣት፣ የተከናወኑ ተግባራት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት ባደረገው…

Read More

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው በክብር ሸኘ

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው በክብር በመሸኘት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህ እና የአሰራር ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባው አቶ ደመቀ መኮንንን በሙሉ ድምፅ በክብር ሸኝቷል። በምትካቸውም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

Read More

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የድሬዳዋ አስተዳደር መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል

ከጥር 13 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ማጠቃለያ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ የድሬዴዋ አስተዳደርም አቶ ተመስገን ጥላሁን በቀጣይ የስራ ዘመንናቸው መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ተመኝቷል። የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ሥርዓት በመከተል ዛሬ…

Read More

የብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ

ከጥር 13 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ በስብሰባዎቹ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታ እንዲሁም ወቅታዊ ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎችን የሚዳስስ ‹ስብራትን መጠገን፣ ለትውልድ መታመን› የሚል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ የፓርቲው መግለጫ ሙሉ ቃል…

Read More

አሁን ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው” ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር የገቡ የሁለተኛ ትውልድ ዲያስፖራዎች

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ያስተላለፍትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ከተማችን ድሬዳዋ በርካታ ዲያስፖራዎች መምጣታቸው ይታወቃል። በዚህም ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ለመጡ እንግዶች አስተዳደሩ የተለያዩ ሁነቶችን በማዘጋጀት ላይ ሲገኝ ትላንትና ምሽትም በክብር ዶ/ር አሊ ቢራ ፖርክ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ለሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ የእራት ግብዣና የባህል ምሽት እየተከናወነ ይገኛል

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጲያውያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ያስተላለፍትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ከተማችን ድሬዳዋ በርካታ ዲያስፖራዎች የመጡ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ለእንግዶች የተለያዩ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ድሬዳዋዊ መስተንግዶ እያደረገ ይገኛል። በዛሬው ዕለት ዲያስፖራዎቹ በከተማዋ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎች የጎበኙ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ በክብር ዶ/ር አሊ ቢራ ፖርክ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና…

Read More

የዳያስፖራው ማህበረሰብ በአገሩ ልማት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይጠበቃል

የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የገቡና በድሬዳዋ የሚገኙ ዲያስፖራዎች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ግዙፍ የልማናት ስራዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል። በተለያዩ የውጭ አገራት ኑሯቸውን ያደረጉና ድሬዳዋ የሚገኙ ዲያስፖራዎች የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ዞንና የነፃ የንግድ ቀጠና ዞን ጎብኝተዋል።በጉብኙቱ ዲያስፖራውን በልማት ስራ እንዲሰማሩ የሚያነሳሳ ስራ መኖሩን መመልከታቸውን ያነጋገርናቸው ዲያስፖራዎች ገልፀውልናል። ቀደም ሲል ኑሯቸውን በባህር ማዶ አድርገው…

Read More

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የ 2016 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል

የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባለፉት አመታት በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ፣ እንዲሁም ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ ተቋሙ በድሬዳዋ ፣ በሀረር እንዲሁም ደግሞ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጂጂጋ ቅርንጫፎችን በመክፈት ፈጣን አገልግሎቶችን ለነዋሪው ህብረተሰብ እየሰጠ ሲሆን በዛሬው እለትም የተቋሙ የ 2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ…

Read More

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በቅርቡ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡ ሚኒስትር ዴዔታዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ÷በቅርቡ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን እንደምታስተናግድ ገልጸው ፥ ለዚህም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ጉባዔውን እንደተለመደው በስኬት ለማስተናገድ ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያም ሆነ መዲናዋ…

Read More