የድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየም አለም አቀፍ ጨዋታን አስተናገደ ።

የድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ አለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን ደረጃ በማሟላት በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከ ዩጋንዳ አቻው ጋር የሚያደርገውን የወዳጅነት አለም አቀፍ ጨዋታውን በማስተናገድ ላይ ነው። የድሬዳዋ ስቴዲየም ወደ ቀደሞ ክብር እና ዝና ለመመለስም አስተዳደሩ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ የስቴዲየሙን የማስፋፊያ እና እድሳት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን በዛሬው እለትም…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጅሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት እና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ያካሄዱት ጨዋታ በድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች 3ለ0 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አሽንፏል።

በእግር ኳስ ጨዋታውም የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት አብላጫውን ጨዋታ በበላይነት የመሩ ሲሆን ክቡር ከንቲባ ከድር ጅሀርን በጨዋታው አንድ ጎል አግብቷል። በአሁኑ ሰዓትም በሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ጨዋታው እየተካሄደ ነው።

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር የእግር ኳስ ጨዋታ ስቴዲየም የፊፋ እና ካፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ አለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን ደረጃ በማሟላት በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ከ ኡጋንዳ አቻው ጋር የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታውን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ነው።

በዚህም የእግር ኳስ ጨዋታ መርሀ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጅሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት እና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሚያካሂዱት የእግር ኳስ ጨዋታ ተጀምሯል ።

Read More

“ ሒጋ “ በሚል ርእስ በኦሮምኛ ቋንቋ የተጻፈ ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ ተመርቋል።

በመጽሐፉ መረቃ ስነስርዓት ላይ የታደሙት የድሬዳዋ አስተዳር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ድሬዳዋ የኪነትና ከያኒያን መፍለቂያነቷ የማይነጥፍ ነው ብለዋል ፡፡ “ ሒጋ “ በሚል ርእስ በኢንጂነር ነስረዲን ሐሰን በአፋን ኦሮሞ ተጽፎ ለአንባቢያን የቀረበው ይሕ መጽሃፍ በሃያ አንድ ምእራፎች ተደራጅቶ በሶስት መቶ ሰባ ገጾች የተዘጋጀ ሲሆን ከተፈጥሮ ተነስቶ ህዋና ምህዋሯን እስከ ፕላኔቶች የዘለቀ የሃሳባት ጥግ የሚጓዝ መሆኑን በምረቃ…

Read More

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 386 ተማሪዎች በደማቅ ስነ-ስርዓት እያስመረቀ።

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ7ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 386 ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 338 በቅድመ ምረቃ፣ 29 በድህረ ምረቃ ትምህርታቸው የተከታተሉ ናቸው። በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባ አደም ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በተለይም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩኒቨርስቲው ለህክምና…

Read More

በሰብዓዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራው ዲያሎግ ሂዩማኒቲ በድሬዳዋ ሲያካሂድ የቆየውን መርሃግብር አጠናቀቀ።

ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ልጆች ፣ ወዳጆች እንዲሁም ከፈረንሳይ ፣ ከጅቡቲ፣ ከኒጀር፣ ከማሊ፣ እንዲሁም ከዩኤስኤን ጨምሮ ከሌሎች የዓለም ሀገራትም የመጡ የዲያሎግ ሂዩማኒቲ አባላት እና ተሳታፊዎች ለተከታታይ ቀናት በድሬደዋ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለት የፕሮግራሙ በመዝጊያ የምሳ ግብዣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቤተመንግስት ተደርጎላቸዋል። በማጠቃለያ መድረኩ…

Read More

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ወደ ስራ መግባቱ ጥቅሙ ለድሬደዋ መስተዳደር ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች ክልሎችም መሆኑ ተገለፀ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር ንግግር ያረጉ ሲሆን ዛሬ ይህ መማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የመለሰ መሆኑን አንስተው፤ ሆስፒታሉ የዩኒቨርስቲው አንዱ ማሰልጠኛ ሆኖ ጎን ለጎንም ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት አጠናክሮ እንዲቀጥል በቀጣይ የሚያስፈልጉ መሰረተ…

Read More

ዜና ታሪካዊው የድሬዳዋ ምድር ባቡር የመንገደኖች ተርሚናል በ 13.5 ሚሊየን ብር ጥገና ሊደረግለት እንደሆነ ተገለፀ

የድሬደዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ከኢትዮጲያ ቅርስ ባለስልጣን መ/ቤት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ታሪካዊውን የድሬዳዋ ምድር ባቡር የመንገደኖች ተርሚናልን ለመጠገን በዛሬው ዕለት የውል ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት አከናወነ፡፡ በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መካኤል እንዳለ የድሬደዋ ምድር ባቡር ረጅም እድሜ ያስቆጠረ በመሆኑና የድሬደዋን ታሪክ የያዘ በመሆኑ ለከተማችን ከፍተኛ…

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

Read More

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው፡- አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት እና የወደፊት ብልጽግናችንን የምናረጋግጥበት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የምክር ቤቱ አባላት የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ኘሮጀክትን…

Read More