በድሬዳዋ ሴቶች ጓዳ ተቀምጠው ዱቄት ከመጠበቅ ይልቅ የራሳቸውን ዱቄት ፋብሪካ ከፍተው እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ

ሚኒስተሩ ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጋር በጋራ በመሆን 11 አምራች ኢንደስትሪዎችን ሲመርቁ ነው። ከተመረቁት ኢንደስትሪዎች መካከል “ባህር ዱቄት ፋብሪካ” አንዱ ሲሆን የፋብሪካው ባለቤት እና ስራ አስኪያጅም ማርያ ሳላ ይባላሉ። ባህር የዱቄት ፋብሪካ በ 37 ሚሊየን ብር ካታል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ፋብሪካ ሲሆን ለ 21 ዜጎችም የስራ እድልን ፈጥሯል። የፋብሪካው…

Read More

“ድሬዳዋ ሰላማዊና ቀንም ለሊትም እንቅስቃሴ ያላት ከተሟ ከመሆኗ በተጨማሪ በኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ መሰረት የጣለች ከተማ ናት”የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው ዕለት 11 የአምራች ኢንደስትሪዎችን መርቀዋል። በዚህም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር በአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀው፤ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ለአካባቢው ማህበረሰብ እየፈጠሩ ከሚገኙት የስራ እድል ባሻገር የውጭ ምንዛሬ እያስገኙ እንደሚገኙ…

Read More

“የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ ኢትዮጵያ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ናት” ሲሉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ ዕድል እንዳቀረበ አፅንኦት ሰጥተው ማንሣታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው…

Read More

በአስተዳደሩ 3ኛዉ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመስከረም 30 ጀምሮ ይሰጣል.. የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

በድሬዳዋ አሰተዳደር 3ኛዉ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመስከረም 30 ጀምሮ እንደሚሰጥ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይሱፍ ሰኢድ በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀዋል። የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከመስከረም 30 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት እንደሚሰጥ ኃላፊው አስታውቀዋል። በክትባት ዘመቻውም በአስተዳደሩ 97,364 ህጻናትን ለመከተብ…

Read More

በአፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተመራ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር የተገነቡ አዳዲስ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመመረቅ እና ለመጎብኘት ድሬዳዋ ከተማ ገቡ

እንግዶቹ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በክብር ወ/ሮ ፈቲያ አደን በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Read More

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የነበረንን ቆይታ አጠናቀን ወደ አዲስ አበባ ተመለሰን የሳይፕረስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብለናል። ሁለቱ ሀገሮቻችን የዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበት ጠንካራ ፍላጎት አለን። በመሆኑም እነዚህን የጋራ አላማዎች ለማራመድ የሚጠቅሙንን ሰፊ አድማስ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል፦ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ( ዶ/ር)

Read More

በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ::

የድሬዳዋ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክት ምዕራፍ ሁለት በገጠር ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የአመራር በቡድን ክህሎት፣በስራ እድል ፈጠራና በስራ ፈጠራ አገልግሎት ዙሪያ የተዘጋጀ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ስልጠናው ከፌደራል ፕሮጀክት ዩኒት እና ከድሬዳዋ ስራና ክህሎት ቢሮ ለተውጣጡ ባለሞያዎች የሚሰጥ ነው። በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ኢሳም ሁሴን የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጠጥ…

Read More

“በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በህዝቡ ርብርብና በአመራር ቁርጠኝኘት የተገኙ ስኬቶች ናቸው”

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በዚህም በጉብኝቱ ኮንቬንሽን ማዕከልን፣ “መሶብ ድሬ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን፣ የእመርታ ቤተ-መፅሀፍን፣ በራስ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን የሚመረምር አልኒቲ (Alinity) የተሰኘ ዘመናዊ ማሽን መረቁ::

ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ የዘመናዊ የደም ተላላፊ በሽታዎች መመርመሪያ ማሽንን በዛሬው ዕለት መርቀዋል። ከዚህ ቀደም ማሽኑ በአስተዳደሩ ባለሞኖሩ ናሙናዎች ወደ ሌሎች ከተሞች እየተላኩ ምርመራ የሚደረግ ሲሆን ይህም ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ከንቲባ ከድር የተናገሩ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር 13ኛው የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

“ዲጂታላይዜሽንና ፈጠራ ለጠንካራ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል 13ኛው የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ በድሬዳዋ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጉባኤው በድሬዳዋ በመካሄዱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ፤ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለአስተዳደሩ ብሎም እንደ ሀገር የተጣለበትን የማህበረሰብ…

Read More