የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5 /2014 በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግሥት የሃገርን ህልውና፣ ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች የመጠበቅ የሕግም ሆነ የሞራል ኃላፊነት እና ግዴታ ያለበት መሆኑን በመገንዘብ፤ የሽብርተኛው ሕውሃት እና የሽብር ግብረአበሮቹ እንቅስቃሴ በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ ጉልህ እና ድርስ አደጋ የደቀነ በመሆኑ፤ ሽብርተኛው ሕውሃት እና የሽብር ግብረአበሮቹ ለዕኩይ አላማቸው መሳካት በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ…


